ትላንት በአዋጅ ቁጥር1249/2013 አንቀፅ 57(1) መሠረት የተቋቋመው “የኢትዮጽያ የፌዴራል ጠበቆች ማህበር” ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንቱን እና ምክትል ፕሬዜዳንቱን መርጧል።
በዚህም ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ኘሬዘዳንት ፤ አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው ደግሞ ምክትል ኘሬዘዳንት ሆነው ተመርጠዋል።
የፍትህ ሚኒስቴር በህጉ በተደነገገው መሰረት ጉባዔውን በመጥራት የማህበሩ ፕሬዘዳንት እና ም/ል ፕሬዘዳፈንት እንዲሁም የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት እንዲመረጡ አድርጓል።
በተመሳሳይ ጠቅላላ ጉባኤው 7 /ሰባት/ የስራ አስፈፃሚ አባላትን መርጧል።
በዚህም መሠረት:-
- ሂሩት መለሠ; 634
- ፊሊጶስ አይናለም; 628,
- ሊቁ ወርቁ; 522,
- ዮሴፍ አዕምሮ;514,
- ሆሳና ነጋሽ; 492,
- ትደነቂያለሽ ተስፋ;424,
- ሰለሞን እምሩ; 418,
የስራ አስፈጻሚ አባል ሆነው ትላንት ተመርጠዋል።